ፋብሪካ አስተዳደር

ለአምራች ድርጅቶች የተዘጋጀ። ከ ፋብሪካ ግብአት ግዢ እስከ ምርት እና ሽያጭ ያለውን የግብአት ፍጆታ እና የግብአት የውህድ ቀመር (Recipe) ፣ ተረፈምርት የመሳሰሉ ስሌቶችን እና የያንዳንዱን ምርት ሙሉ ታሪክ መከታተያ በተጨማሪም የምርት ጥራት ማብቅያ ግዜ የመሳሰሉ ክንውኖችን ማስተዳደር ያስችላል።

ፕሮጀክት አስተዳደር

እንደኮንስትራክሽን ላሉ በጣም ውስብስብ ፕሮጀክቶች በቀላሉ የስራ ክንውን ለመከታተል የሚያስችል። ከሁሉም ሰራተኞች ጋር ባካል መገናኘት ሳያስፈልጎ የፈለጉትን ሰራተኛ የፈለጉት የስራ ዘርፍ ላይ መመደብ ፣ ውጤት መከታተል ፣ የግል እና የቡድን ማስታወሻዎችን መላክ የመሳሰሉ ዘመናዊ መፍሄዎችን የያዘ።

ንብረት አስተዳደር

ለትላልቅ መግስት እና የግል ድርጅቶች ፣ እርዳታ ድርጅቶች ለመሳሰሉ ተቋማት ታስቦ የተዘጋጀ። በቀላሉ የድርጅቶን ንብረት በመመዝገብ ለድርጅቱ ሰራተኞች ፍቃድ መስጠት። ለምሳሌ፥ ኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች ፣ መጓጓዣ መኪና እና የመሳሰሉት። ለሚሰጡት ንብረት በቀላሉ የቀን ገደብ መስጠት ፣ ማገድ እና ሌሎችንም ስራ አቅላይ ቴክኖሎጂዎችን ያሟላ።

የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር

እንደ ሪልእስቴት ላሉ ተቋማት እጅግ ጠቃሚና ወሳኝ የደንበኛ ግንኙነት ማስተዳደርያ መተግበርያ ያሟላ ሲሆን የደንበኛዎን የመግዛት አቅምና መች ሊገዙ እንደሚችሉ በመረጃ የተደገፈ የሽያጭ ስራት ለመዘርጋት ያስችላል።

ለካፌ ፣ ባር እና ሬስቶራንት ፣ ለሆቴሎች

ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደ ካፌ ፣ ባር እና ሬስቶራንት ፣ ሆቴሎች እና ሌሎችም የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ኩሽና አስተዳደር እና መስተንግዶ ክትትል የመሳሰሉ ልዮ መፍትሄዎች

ለሁሉም ነጋዴዎች

ከጥቃቅን እና አነስተኛ ነጋዴዎች እስከ ትልቅ ሱፐር ማርኬት ፣ ፋርማሲ እና ማንኛውም የንግድ ድርጅት። ከ ግለሰብ አንስቶ ብዙ ቅርንጫፍ ያላቸው ንግድ ድርጅቶች, የሁሉንም አቅም ያማከለ መፍትሄ

Recent Posts

Recent Posts