ደንበኛ መስተንግዶ
ባሉበት(Remote)
ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት(Front Desk)
12 ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች
0+ አመት
6 ሰአት /በቀን
1000 ብር/በወር
10% ኮምሽን
በዚህ ስራ ላይ መሰማራት ሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለስራው ከመወዳደሩ አስቀድሞ መረዳት ያለባቸው ነገር፣ በመጀመርያ እራሳችሁን ለመማር ዝግጁ ማረግ አለባችሁ። ምክኒያቱም በ ደንበኛ መስተንግዶ ላይ በሚሰሩበት ወቅት ደንበኛው ስለ ድርጅታችን አገልግሎት እና አሰራር ለሚያነሱት ማንኛውም አይነት ጥያቄ ይሁን ሀሳብ ተገቢውን እና የተሟላ ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለቦት።
ሁለተኛ ሰአት ማክበር ግዴታ ነው። ከስራው ዘርፍ አንፃር በ 4 ሽፍት ሚሰራ አንደመሆኑ መጠን በዚ ስራ ላይ ከተቀጠሩበት ቀን አንስቶ በሚመደብሎ የሰአት ምድብ 15 ደቂቃ አስቀድመው በስራው ገበታ ላይ መገኘት ይኖርቦታል።
በዚ ስራ ላይ ለመወዳደር ሚያስፈልገው ዋንኛው መስፈርት ተነሳሽነት እና ለድርጅቱ ስኬት የግል ድርሻ ለመወጣት ሚፈልግ ቁርጠኛ ሰራተኛ ነው። ምንም አይነት የትምህርት ማስረጃ ባይጠይቅም ስራው ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ስለሆነ የኮምፒውተር ቤዚክ አገልግሎቶችን መጠቀም እና ማስረዳት መቻል አለቦት።
በድርጅታችን ስር ተቀጥረው በሚሰሩበት ሰአት ድርጅታችን እርሶን ለስራው ብቁ ለማድረግ በመጀመርያ ሙሉ የመለማመጃ ነፃ ኮርሶችን ይሰጣል.!
በዘመናዊ ነጋዴ ኮርፖሬሽን ተቀጥረው ሚሰሩ ማንኛውም ሰራተኞች ለድርጅቱ ህግ እና መመርያዎች መገዛት ይኖርባቸዋል። እነኝን ህጎች ተላልፎ የሚገኝ ሰራተኛ ያለምንም ማስተንቀቅያ ከስራው ገበታ ሊባረር ይችላል።