የስራ ዝርዝር
ዲፓርትመንት

ሽያጭ(Sales Agent)

ስራ ቦታ

በተመረጡ ከተሞች

ስራ አይነት

ሽያጭ(Sales)

የትምህርት መስፈርት

ዲግሪ በ አካውንቲንግ ወይም ማርኬቲንግ

የስራ ልምድ

2+ አመት

የስራ ሰአት

በፈለጉት ሰአት

ደሞዝ

በመጀመርያ ወር 100% ኮሚሽን

ተጨማሪ ጥቅም

20% ኮምሽን በየወሩ ሚከፈል

የሥራ መስፈርቶች

በዚህ ስራ ላይ መሰማራት ሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለስራው ከመወዳደሩ አስቀድሞ መረዳት ያለባቸው ነገር፣ በመጀመርያ እራሳችሁን ለመማር ዝግጁ ማረግ አለባችሁ። ምክኒያቱም በ ድርጅታችን ሚሰጠው አገልግሎት ለማህበረሰባችን አዲስ እንደመሆኑ በመጀመርያ እኛን በስኬታማ መንገድ ለመወከል ቀድመው ስለድርጅቱ አገልግሎት ሙሉ መረጃ እና እውቀት እንዲኖሮት ያስፈልጋል።

ሁለተኛ የሽያጭ ስራውን በ ኤጀንትነት ከኛጋር እንዲሰሩ ምንፈልጋቸው ሰራተኞች በእሁን ሰአት በአካውንቲንግ እና ማርኬቲንግ ምሩቆችን ሲሆን እነሱም ቢያንስ የ 2 አመት የስራ ልምድ ሊኖራቸው ይገባል።

ማንን ነው ምንፈልገው?

በዚ ስራ ምድብ የምንፈልገው ሰራተኛ በአካውንቲንግ ወይም ማርኬቲንግ ምሩቅ ሲሆን የድርጅቱን አገልግሎቶች እኛን ወክለው ሽያጭ ማከናወን መቻል አለባቸው።

  • እድሜ፦ 18+.
  • ፆታ፦ ወንድ/ሴት
  • የትምህርት ደረጃ፦ ዲግሪ በ አካውንቲንግ ወይም ማርኬቲንግ
  • ባህሪ፦ ንቁ እና ቀልጣፋ(sociable)
  • ስራ ቦታ፡ በዝርዝር በተቀመጡ ከተሞች

ድርጅታችን ምን ሊያደርግሎት ይችላል?

በድርጅታችን ስር ተቀጥረው በሚሰሩበት ሰአት ድርጅታችን እርሶን ለስራው ብቁ ለማድረግ በመጀመርያ ሙሉ የመለማመጃ ነፃ ኮርሶችን ይሰጣል.!

  • ጥሩ የማሳመን እና የማስረዳት ክህሎት ኖሮት በወር ውስጥ እኛ ያስቀመጥነውን የዝቅተኛ የሽያጭ መስፈርት ለሚያሟሉ ሰራተኞች እድገት እንሰጣለን
  • በ በአል ወቅት ልዩ ጥቅማጥቅም
  • ሽያጭ አከናውነው በርሶ በኩል የመጡት ደንበኞች የረጅም ግዜ ደንበኛ ከሆኑ ዳጎስ ያለ ልዩ ተጨማሪ ክፍያ

የድርጅታችን ህግ እና መመርያዎች:

በዘመናዊ ነጋዴ ኮርፖሬሽን ተቀጥረው  ሚሰሩ ማንኛውም ሰራተኞች ለድርጅቱ ህግ እና መመርያዎች መገዛት ይኖርባቸዋል። እነኝን ህጎች ተላልፎ የሚገኝ ሰራተኛ ያለምንም ማስተንቀቅያ ከስራው ገበታ ሊባረር ይችላል።

  • በተሰማሩበት የስራ ምድብ ላይ በድርጅቱ ለሚቀርቡ የአሰራር መመርያዎች እና ህጎች መገዛት ግዴታ ሲሆን በራሶ የስራ ምድብ ካሉ ሰራተኞች በስተቀር ለናንተ ምድብ ተብሎ ሚዘጋጁ ማንኛውንም አይነት መረጃ ፣ እቃ ወይም ንብረት ፣ ከተመደበለት የስራ ዘርፍ ውጭ ማጋራትም ሆነ ለግል ጥቅም ማዋል አይቻልም።
  • የድርጅቱንም ሰራተኞችም ሆነ የደንበኞችን ማንነት ሚገልፆ መረጃ መቀያየር ወይም ማጋራት አይቻልም። ይህን ሲያደርግ የተገኘ ሰራተኛ ወድያው ከስራው ገበታ ከመነሳትም አልፎ ህጋዊ እርምጃ ድርጅታችን ሚወስድ መሆኑን እናሳስባለን!
  • ሰአት አለማክበር ያለምንም ድርድር ከስራ ገበታ የሚያባር መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።