መተግበርያ አጠቃቀም/Technical

እጅግ በጠም! ዘመናዊ ነጋዴ ስሙ ንግድ ሚል ቃል ያካተተ ቢሆንም በንግድ አለም ላይ ለተሰማሩ ግለሰብም ሆነ ድርጅት እና ከንግድ አለም ዉጭ ላሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ሚሰጥ መተግበርያ ነው። ለምሳሌ ምንም ንግድ ማያከናውን ተቀጥሮ ሚሰራ አንድ ግለሰብ አነስተኛውን የዘመናዊ ነጋዴ ፓኬጅ በመግዛት በለተለት ሚያከናውናቸውን ወጪዎች መተግበርያውን በመጠቀም መመዝገብ ይችላል።

ዘመናዊ ነጋዴ የደንበኞቻችንን የመጠቀም አቅም ለማጎልበት በማሰብ መተግበርያው ገና እንደ ሀሳብ ሲነደፍ አንስቶ ሙሉ አገልግሎቱን ለያንዳንዱ የሙያ ዘርፍ እና ድርጅት ፍላጎት ሚያሰፈልገውን የመለማመጃ ሙሉ ትምህርት በ ዘመናዊ ነጋዴ አካዳሚ በነፃ ማዘጋጀቱን ሲያበስር በደስታ ነው። ይህን አካዳሚ በመቀላቀል መተግበርያውን ለመጠቀም በሚመዘገቡበት ወቅት ሚያገኙትን የ 14 ቀን ነፃ የግዜ እፍይታ በመጠቀም በነኚህ ቀናት ውስጥ አካዳሚው ሙሉ እውቅና ያጎናፅፎታል።

ከመለማመጃው ግዜም በውሃላ ቢሆን ከ አካዳሚው ውጭ ሚያስቸግሮት ነገር ካለ የቻት አገልግሎቱን በመጠቀም ወድያው መፍትሄ ያገኛሉ።

የክፍያ ተመን እና ድጋፍ/Pricing & Support

ድርጅታችን በተቻለ መጠን የደንበኞችን ፍላግት እና የመግዛት አቅም ያማከለ የክፍያ አማራጮችን አዘጋጅቷል ነገር ግን እርሶ ሚፈልጉትን መፍትሄ ማግኘት ካልቻሉ በቀላሉ ከዚ ስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ሚፈልጉትን አማራጭ ለኛ ማሳወቅ ይችላሉ። በአጭር ሰአት የድርጅታችን ሽያጭ ክፍል ሰራተኞች ከናንተጋር በመገናኘት አፋጣኝ መፍትሄ እናቀርባለን።

ይህን በመጫን ሀሳቦን በተዘጋጀው ፎርም ላይ ሞልተው ይላኩልን። 

የደንበኞች ድጋፍ/Customer Support

በድረገጻችን መግቢያ ላይ እንደሚመለከቱት የቻት ወይም የ ቀጥታ የመጻጻፍያ ቦታ ስላለን በየትኛውም ሰአት እና ግዜ ቅር ያሎት ወይም ያልተረዱት ነገር ካለ በቀላሉ የቻት አማራጩን በመጠቀም በሰለጠኑ የደንበኛ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞቻችን ጋር በመገናኘት ወድያው ቅሬታዎ እና ችግሮን መፍታት ይችላሉ።

ይህ ሳይሆን ሲቀር ወይም በሰአቱ መፍትሄ ማግኘት ካልቻሉ የድጋፍ ትኬት በመክፈት ከድርጅቱ ሲኒየር ባለሞያዎች በአጭር ግዜ ምላሽ ያገኛሉ።

የድጋፍ ትኬት ለመክፈት ይህን ይጫኑ።

ዘመናዊ ነጋዴ የደንበኞቻችንን የመጠቀም አቅም ለማጎልበት በማሰብ መተግበርያው ገና እንደ ሀሳብ ሲነደፍ አንስቶ ሙሉ አገልግሎቱን ለያንዳንዱ የሙያ ዘርፍ እና ድርጅት ፍላጎት ሚያሰፈልገውን የመለማመጃ ሙሉ ትምህርት በ ዘመናዊ ነጋዴ አካዳሚ በነፃ ማዘጋጀቱን ሲያበስር በደስታ ነው። ይህን አካዳሚ በመቀላቀል መተግበርያውን ለመጠቀም በሚመዘገቡበት ወቅት ሚያገኙትን የ 14 ቀን ነፃ የግዜ እፍይታ በመጠቀም በነኚህ ቀናት ውስጥ አካዳሚው ሙሉ እውቅና ያጎናፅፎታል።

ከመለማመጃው ግዜም በውሃላ ቢሆን ከ አካዳሚው ውጭ ሚያስቸግሮት ነገር ካለ የቻት አገልግሎቱን በመጠቀም ወድያው መፍትሄ ያገኛሉ።

ፈቃድ/License

ውል እና ሁኔታዎች ያስፈለገበት ዋንኛ ምክንያት ይህ የዘመናዊ ነጋዴ መተግበርያ አገልግሎቱን ሚያቀርበው በኪራይ መልክ ሲሆን በሁለት የክፍያ አማራጭ ቀርቧል። ወርሁዊ እና አመታዊ ክፍያ አማራጭ ሲሆን የክራይ አገልግሎቱ ህጋዊ እንዲሆን እና የድርጅታችንን የባለቤትነት እውቅና ለማስጠበቅ የውል እና ሁኔታዎች መዘጋጀት ግድ ያደርገዋል።

ደንበኞች ይህን ውል እና ሁኔታ ምዝገባቸው ከመጠናቀቁ በፊት መተግበርያችን ውሉን ማንበባቸውን እና በሁኔታዎቹ መስማማታቸውን እንዲያረጋግጡ ያስገድዳል።