ድርጅቶን ዘመናዊ ነጋዴ ላይ ለማስመዝገብ

ለአዲስ ድርጅት ምዝገባ #

  1. በመግቢያ ገጽ ላይ ይመዝገቡ ሚለውን ይጫኑ ።
  2. ድርጅቶን ማስመዝገብ 3 ደረጃዎችን ያካትታል፤ የድርጅት ዝርዝሮች፣ የግብር ዝርዝሮች እና የባለቤት ዝርዝሮች።
  3. የድርጅት ዝርዝሮች፥ ተዛማጅ መስኮችን ይሙሉ፤ ተገቢውን ምንዛሪ ይምረጡ እና የሰዓት ዞን፤ ቀጣይ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
  4. የግብር ዝርዝሮች፡ ቢያንስ አንድ የታክስ ስም እና የታክስ ቁጥር መሙላት አለቦት። ታክስ ቫት ቁጥር ነው። ይህም ለተለያዩ ንግድ ፍቃዶች የተለያየ የቫት ፐርሰንት ስሌት ስላለ ድርጅቶን ሚወክለውን ይሙሉ። ዝርዝሮችን ይሙሉ እና በሚቀጥለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
  5. የባለቤት ዝርዝሮች፡ የተጠየቁ ዝርዝሮችን ያቅርቡ። የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል መተግበርያው ላይ ለመግባት ጥቅም ላይ ይውላሉ ስለዚህ ማስታወስዎን ያረጋግጡ።
  6. በዚህ ምዝገባ ወቅት የተፈጠረው ባለቤት የንግዱ አስተዳዳሪ ይሆናል። ተጨማሪ አስተዳዳሪ ከተጠቃሚ አስተዳደር ክፍል ሊመዘገብ፨ሊስተካከል፨ሊሰረዝ ይችላል።
  7. የመመዝገቢያ ቁልፍን ጠቅ ያድርጉ እና ከተሳካ ምዝገባ በኋላ ወደ የመግቢያ ማያ ገጽ ይዛወራሉ። በባለቤቱ የተጠቃሚ ስም/የይለፍ ቃል ይግቡ።

    ማሳሰብያ፥ ለምዝገባ ሚጠቀሙት የባለቤት ስም ድርጅቶ ዋና ሀላፊ መሆን አለበት ክፍያም በተመሳሳይ ስም ነው መከፈል ሚችለው።

 

Powered by BetterDocs