የደንበኛ ምድቦች

Table of Contents

የደንበኛ ምድቦች #

በደንበኛ ምድቦች ደንበኛን እንደ የችርቻሮ ደንበኞች፣ የጅምላ ሻጭ ደንበኛ፣ ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦች እና ማንኛውንም የሚፈልጉትን ምድብ መሰየም ይችላሉ።

  1. አዲስ“የደንበኛ ምድብ” ለማከል ወደ መገኛ አማራጮች በመሄድ የደንበኛ ምድቦች ሚለውን ይምረጡ በመቀጠል ያስገቡ ሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።
  2. የደንበኛ ቡድን ስም እና ስሌት መቶኛ የሚጠይቅ ፎርም ወደፊት ብቅ ይላል።
    የመሸጫ ዋጋን ለማስላት ስሌት መቶኛ ጥቅም ላይ ይውላል።

ለምሳሌ:

ለአንድ እቃ የተዘጋጀው የመሸጫ ዋጋ 2500 ብር ነው እንበል

የደንበኛ ምድብ ስም = ጓደኛ

ስሌት መቶኛ = -20

ማስታወሻ -20 (የመቀነስ ምልክትን አስተውሉ) ወይም 20 = +20% ሊያዘጋጁት ይችላሉ።

የደንበኛ ቡድን እንደ ጓደኛ የተመደበ ደንበኛ ዘርፍ ፈጥረዋል ።

አሁን ወደ POS ወይም መሸጫ ማያ ይሂዱ። ደንበኛው ዘርፍ ይምረጡ እና ምርቱን ያክሉ።

ለእቃው የተቀመጠው የመሸጫ ዋጋ 2500 – 20% = 2000 ብር እንደሚሆን ያስተውላሉ

የደንበኛ ምድብ የሚሰራው በዚህ መንገድ ነው።

የደንበኞች ምድብ የውስጥ ስሌት ይሰራል እና የስሌቱን መቶኛ ለሽያጩ ዋጋ ይተገበራል። በክፍያ መጠየቂያው ወይም በ POS ስክሪኑ ላይ የተለየ ቅናሽ አያሳይም።

ይህ ባህሪ ችርቻሮ፣ ጅምላ ወይም የተለያዩ የደንበኛ ምድቦች ሲኖርዎት በጣም ጠቃሚ ነው።

ለተለያዩ የደንበኞች ምድብ የደንበኛ ምድቦች ሪፖርት ወይም በሌላ መልኩ የችርቻሮ እና የጅምላ ደንበኞች ምድብ ካላቹ የትኛው የደንበኛ ምድብ የበለጠ ሽያጭ እንደሚሰጥ ማየት ትችላላቹ።

 

 

Powered by BetterDocs