የኮሚሽን ተከፋይ አባላት አገልግሎት ለመጠቀም

የኮሚሽን ተከፋይ አባል ለብዙ ድርጅቶች ጠቃሚ ነው። ድርጅቶች ለሽያጭ ወኪሎች/ለኮሚሽን አባል፣ ኮሚሽን በሚያመጡት እያንዳንዱ ሽያጭ ይከፍላሉ።

የኮሚሽኑ ወኪል አይነት ማዘጋጀት እና መምረጥ #

በመደበኛነት የኮሚሽን ወኪል አባል ስራ ላይ አይውልም። በማስተካከያ ፡ የንግድ ማስተካከያዎች ላይ ሽያጭ ሚለው ላይ በመግባት ኮሚሽን ተከፋይ አባል ሚለውን የምርጫ ዝርዝር ላይ በመንካት አገልግሎቱን ወደ ስራ ማስገባት ይችላሉ።

3 የተለያዩ ዓይነቶችን ታያላቹ

  1. መተግበርያ ተጠቃሚ፡ ይህ አማራጭ ጥቅም ላይ ከዋለ የዘመናዊ ነጋዴ ተጠቃሚው በራሱ ለገቡ ሽያጮች እንደ ኮሚሽን ወኪል ይቆጠራል። ተጠቃሚው ሽያጩን ሲያስገባ ለሽያጩ ኮሚሽን ያገኛል ማለት ነው።
  2. ከተጠቃሚ ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ፡ ይህ አማራጭ ስራ ላይ ከዋለ በ POS እና በሽያጭ ማከናወኛው ላይ በድርጅቶ ውስጥ ያሉትን የተጠቃሚዎች ዝርዝር ያያሉ። ሽያጩን የሚመዘግበው ተጠቃሚ ከተጠቃሚዎች ዝርዝር ውስጥ ይመርጣል።
  3. ከኮሚሽን ወኪል ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ፡ ይህ አማራጭ ስራ ላይ ከዋለ በPOS እና ሽያጭ ማከናወኛ ላይ በድርጅቶ ውስጥ ያሉትን “የሽያጭ ኮሚሽን ወኪሎች” ዝርዝር ያያሉ። ሽያጩን የሚመዘግበው ተጠቃሚ ከሚታየው “የሽያጭ ኮሚሽን ወኪሎች” ዝርዝር ውስጥ የኮሚሽኑን ወኪል ይመርጣል።

እንደ ድርጅቶ መስፈርት አማራጩን ይምረጡ።

የኮሚሽኑ መቶኛ ማስገባት #

የተጠቃሚን ወይም የሽያጭ ኮሚሽን ወኪልን በሚመዘግቡ ሰአት ወይም መረጃቸውን በሚያስተካክሉበት ወቅት ኮሚሽን % ማስገባት ይችላሉ።

የኮሚሽኑ መጠን ማስላት፡- #

የኮሚሽኑን መጠን ለማየት ወደ ሪፖርቶች -> የሽያጭ ተወካይ ሪፖርት ይሂዱ።

የኮሚሽኑን መጠን ለማየት የሚፈልጉትን ተጠቃሚ ይምረጡ።

ሲመርጡ የጠቅላላ ሽያጭ፣ ጠቅላላ የሽያጭ ኮሚሽን እና አጠቃላይ ወጪን ዝርዝር ማጠቃለያ ያሳየዎታል። እንዲሁም፣ ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ ሁሉንም ግብይቶች ይዘረዝራል።

ማሳሰቢያ፡ የሽያጭ ኮሚሽን ያለ መላኪያ ወይም ታክስ ይሰላል። የሽያጭ ኮሚሽኖች ከዕቃዎቹ ሽያጭ ነው እንጂ እንደ ታክስ፣ ጭነት፣ ማጓጓዣ፣ አያያዝ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ወጪዎች አይደሉም።

የኮሚሽን ክፍያ #

የኮሚሽኑን መጠን ካታወቀ በኋላ ዘመናዊ ነጋዴ ለኮሚሽኑ ክፍያ ለመፈጸም 2 መንገዶች አሉት።

ወጪን በመጠቀም #

  • ኮሚሽኑን ከሽያጭ ተወካይ ሪፖርት አስሉ እና መጠኑን ከከፈሉ በኋላ በወጪ መሙያው ውስጥ እንደ ወጪ ያስገቡ።
  • ወጪዎች ፥ ወጪን ማስገባት ፥ የወጪ ምድብ ሚለው ላይ ካሉት አማራጮች ይምረጡ

የሰው አስተዳደር ሞጁል በመጠቀም #

የሰው አስተዳደር ሞጁሉን ይጠቀሙ
በሰው አስተዳደር ሞጁል ውስጥ ለተጠቃሚ የደመወዝ ክፍያ ሲፈጥሩ የሽያጭ ኮሚሽኑን በራስ-ሰር ያካትታል።
የሽያጭ ኮሚሽን እንደ Payroll-Components ይታያል ይህም የድርጅት ባለቤት እና ተጠቃሚው ሁለቱም የኮሚሽኑን ዝርዝሮች እንዲያውቁ ይረዳል።

Powered by BetterDocs