በ ዘመናዊ ነጋዴ ውስጥ የክፍያ መለያዎች ምንድን ናቸው? #
የክፍያ ሂሳቦች ለምሳሌ የባንክ ሂሳብ ናቸው። ከአንድ የክፍያ አካውንት ወደ ሌላ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ በክፍያ ሒሳብ ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ማስገባት፣ ለአቅራቢው መክፈል ወይም ከደንበኛ የተቀበለውን ገንዘብ ሚፈልጉት አካውንት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
የክፍያ መቀበያ አካውንት ስራ ላይ ማዋል #
- ወደ ማስተካከያዎች -> የድርጅት መረጃ ማስተካከያ -> ሞጁሎች ይሂዱ
- የክፍያ ‘አካውንት’ አማራጭን ይምረጡ
- ይመዝግቡ።
- ከመዘገቡ በኋላ “የክፍያ መቀበያ አካውንት” አማራጭ በግራ የአሰሳ አማራጭ ላይ ይታያል.
የክፍያ አካውንት ዓይነት እና ነጠላ ዓይነት #
ወደ የክፍያ አካውንቶች ይሂዱ -> አካውንቶችን ይዘርዝሩ -> የአካውንት ዓይነቶች
የአካውንት አይነት፡ የአካውንት አይነት ለማስገባት ያስገቡ የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ እና የአካውንቱን አይነት ስም ያስገቡ። የወላጅ አካውንት አይነት ሳይመረጥ ያቆዩት።
የነጠላ/(የበታች ልጅ) አካውንት አይነት፡ የነጠላ አካውንት አይነት ለማስገባት ያስገቡ የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ፡ የነጠላ አካውንት አይነት ስም ያስገቡ እና የወላጅ አካውንት አይነትን ይምረጡ።
አካውንት ሲያስገቡ እንደፍላጎትዎ የአካውንቶ አይነት መምረጥ ይችላሉ።
የክፍያ አካውንቶችን መፍጠር #
የክፍያ አካውንት ለመፍጠር ወደ የክፍያ አካውንቶች ይሂዱ -> አካውንቶች ዝርዝር ፣ ያስገቡ የሚለውን ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ
እንደ ስም፣ የአካውንት ቁጥር፣ የአካውንት አይነት፣ የመክፈቻ ባላንስ ሒሳብ፣ የአካውንት ዝርዝሮች እና ማስታወሻዎች ያሉ ሁሉንም ዝርዝሮች ይሙሉ።
የአካውንት ዝርዝሮች፡ እዚህ እንደ ዩፒአይ መታወቂያ፣ SWIFT ኮድ፣ BIN ቁጥር፣ ወዘተ የመሳሰሉ ተጨማሪ የአካውንት ዝርዝሮችን ማስገባት ይችላሉ።
በክፍያ አካውንቶች መካከል ገንዘብ ማስተላለፍ; #
በክፍያ አካውንቶች መካከል ገንዘቦችን ማስተላለፍ ይችላሉ.
በክፍያ አካውንቶች -> ዝርዝር አካውንቶች ውስጥ፣ ፈንድ ማስተላለፍን ጠቅ ያድርጉ።