የክምችት ማስተካከያ #
የክምችት ማስተካከያ በክምችት ውስጥ ያሉትን እቃዎች እንዲቀንሱ ይረዳዎታል፣ በማንዋል መንገድ የክምችት ማስተካከያዎችን ማስገባት ይችላሉ። በአጠቃላይ የተበላሹ ክምችቶች ለማጥፋት ወይም ከክምችት ከተወሰደ በኋላ መጠኑን ለማስተካከል ይጠቅማል።
የክምችት ማስተካከያ ለመፍጠር
- መጀመሪያ ወደ “ክምችት ማስተካከያ አስገቡ” ይሂዱ
- የድርጅት ቦታ እና ቀን ይምረጡ
- የማስተካከያ ዓይነት (መደበኛ ወይም ያልተለመደ) ይምረጡ። መደበኛ ወይም ያልተለመደ በአጠቃላይ ማስተካከያ ለመመደብ ጥቅም ላይ ይውላል.
በአጠቃላይ መደበኛ ማስተካከያ ትርጉም፡ ለተለመዱ ምክንያቶች ለምሳሌ ፈሶ መጠኑ ሲቀንስ ወዘተ ማስተካከል።
ያልተለመደ ትርጉም፡ እንደ እሳት፣ አደጋ ፣ ወዘተ ባሉ ምክንያቶች ማስተካከል።
እቃውን ለመቀነስ የሚፈልጉትን እቃዎች እና መጠን ይሙሉ።
የተመለሰው ጠቅላላ መጠን፡- አንዳንድ ጊዜ ከተጎዱት ክምችቶች የተወሰነ መጠን መልሰው ማግኘት ይችላሉ፣ ለምሳሌ ከኢንሹራንስ ይገባኛል፣ ካደጋ የተረፉትን መሸጥ ወዘተ። ምንም ነገር ካልተረፈ በቀላሉ “0” ያደርጉታል። ኪሳራ ሪፖርት, ወደ ጠቅላላ ትርፍ / ኪሳራ ሪፓርት ውስጥ ይመዘገባል.
ለእያንዳንዱ እቃ የገቡት መጠኖች ካሉት መጠኖች ይቀነሳሉ።
በ “እቃ ክምችት ማስተካከያ ሪፖርት” ውስጥ የክምችትን ማስተካከያ ዝርዝሮችን ማየት ይችላሉ.
እንዲሁም፣ የክምችት ማስተካከያ በትርፍ እና ኪሳራ ሪፖርት (ት እና ኪ ሪፖርት) ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል። “ጠቅላላ የክምችት ማስተካከያ” መጠን ከ (ትርፍ እና ኪሳራ ሪፖርት) ይቀናነሳል እና “ጠቅላላ የተገኘ ክምችት” መጠን ወደ ትርፍ እና ኪሳራ ሪፖርት ይመዘገባል.