የእቃ ጊዜ የሚያበቃበት እና ተዛማጅ ማስተካከያዎች

ለእቃዎች የሚበላሹበትን ጊዜ ማንቃት #

 1. የሚበላሹበትን ቀን ለማንቃት ወደ ማስተካከያ ፡ከዛ የድርጅት መረጃ ማስተካከያ ፡በመቀጠል የእቃ ምርጫ ላይ ይሂዱ። እና እቃ ሚበላሹበትን ቀን መፍቀድ የሚለውን አመልካች ሳጥኑ ላይ ምልክት ያድርጉ።
 2. ይህን ፍቃድ በሚሰጡበት ግዜ ፣ “የእቃው ማብቂያ ጊዜ አስገቡ” ወይም “የፋብሪካው ምርት ቀን እና የሚያበቃበት ጊዜ አስገቡ” የሚለውን መምረጥ ይችላሉ።
  • የሚበላሹ እቃዎች የማብቅያ ግዜ ያስገቡ: የዕቃውን የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ በቀጥታ በግዢ ስክሪን ላይ ማስገባት ከፈለጉ ይህንን አማራጭ ይምረጡ።
  • የተመረተበትን እና የሚበላሽበትን ቀን ያስገቡ: የእቃውን ምርት ቀን እና የሚበላሽበትን ቀን ማስገባት ከፈለጉ ይህንን አማራጭ ይምረጡ። በማምረቻው ቀን እና በማብቂያ ጊዜ ላይ በመመስረት የማለቂያውን ቀን በራስ፡ሰር ያሰላል። እና ይህ የማለቂያ ቀን ሊስተካከል ይችላል። በእቃ ማስገብያ ወይም ማስተካከያ እስክሪን ውስጥ ለእቃው የማለቂያ ጊዜ ማስገባት አለቦት። እና የማምረቻው ቀን በ ዕግዢ ማስገቢያ ገጽ ውስጥ መሞላት አለበት።
 3. በእቃው ማብቅያ ግዜ በዚህ አማራጭ አንድ እቃ የአገልግሎት ጊዜው ሲያልቅ ምን ማድረግ እንዳለበት ቀድሞ ማዘጋጀት ይችላሉ።
  • መሸጥ ቀጥሉ: የጥራት ማብቅያ ግዜው ካለፈ በኋላም እቃውን መሸጥ እንዲቀጥል ከፈለጉ ይህንን አማራጭ ይምረጡ።
  • መሸጥ ያቁሙ ከተጠቀሰው ቀን ቀደም ብለው: እቃውን መሸጥ ለማቆም ይህን አማራጭ ይምረጡ። ከጥራት ማብቅያው ቀድሞ ማገጃ ቁጥር መግለጽ አለቦት (ይህም መሸጥ ለማቆም የቀናት ብዛት ነው)
 4. የክምችት አካውንቲንግ ዘዴ: ይህ ባህሪ እቃው የሚሸጥበትን መንገድ ለማዘጋጀት ይጠቅማል።
  • መጀየመይ (መጀመርያ የገባ መጀመርያ ይወጣል): በዚህ ውስጥ አሮጌው ክምችት በቅድሚያ መሸጥ አለበት።
  • መጨየመይ (መጨረሻ የገባ መጀመርያ ይወጣል): በዚህ ውስጥ በጣም የቅርብ ጊዜ የግዢ ክምችት ቀድሞ መሸጥ አለበት።

ለምሳሌ፡
1። 20 ፍሬ እቃዎችን በሰኔ 20 2014 ይግዙ። 10ቀን ለጥራት ግዜ ማብቅያው ፣ ሚበላሸው በ በሰኔ 30 2014
2። ሰኔ 23 2014 20 ፍሬ ተመሳሳይ እቃ ይግዙ። የማለቂያ ቀን ሚበላሸው በ ሀምሌ 08 2014
3። ዛሬ 22 ፍሬ ሸጡ።
የክምችት አካውንቲንግ ዘዴ መጀየመይ ከሆነ =ከዚያም በ  ሰኔ 20 2014 የተገዛው እቃ በ 20 ፍሬ ይቀንሳል እና ከዚያ በኋላ በ ሰኔ 23 2014 የእቃ ግዢ በ 2 ፍሬ ይቀንሳል።
ስለዚህ በክምችት ውስጥ፣ ከ ሰኔ 23 2014 ላይ 18 ፍሬ እቃዎች ይኖረናል።
የክምችት አካውንቲንግ ዘዴ መጨየመጀ ከሆነ =ከላይ ያለው ተቃራኒ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡ ለዚ የሂሳብ አሰራር ዘዴ እቃውን ከመሸጥዎ በፊት አስፈላጊውን የሂሳብ አሰራር ዘዴ ማዘጋጀት አለብዎት።

የክምችት ጥራት ማብቂያ ጊዜ ሪፖርት #

 1. ወደ ሪፖርቶች ይሂዱ ሚበላሹ ክምችቶች ሪፖርት
 2. እዚህ የክምችት “ምድብ”፣ ብራንዶችን፣ “የክምችት ጥራት ማብቂያ ቀን”በመሳሰሉ አማራጮች መረጃውን ማጣራት ይችላሉ
 3. የቀረውን ክምችት እና የማብቂያ ጊዜን ለመቀየር አስተካክሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
 4. የተረፈው ክምችት ከተቀነሰ የነጠላ ግዢ ዋጋ በዚሁ መሰረት ይስተካከላል።

የክምችት ጥራት ጊዜ የሚያበቃበት ቀን ማሳወቅያ፡ #

-የክምችት ጥራት አገልግሎት ማብቂያ ማስጠንቀቂያ በመነሻ ገጽ ታችኛው ክፍል ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ በቅርብ ጊዜ የሚያልቁ እቃዎችን ዝርዝር ያሳያል።
– ጊዜው የሚያበቃበት ቀን ሚታይበትን የቀን አቀራረብ ለመሙላት ወደ ማስተካከያዎች ፣ድርጅት መረጃ አስተዳደር በመቀጠል እቃ ሚለው ምርጫ ላይ በመግባት በመሙያው ፎርም ላይ የቀን ገደቡን ያስገቡ።

በክፍያ መጠየቂያው አታችመንት ላይ የእቃ ጥራት ማብቂያ ቀንን እንዲያሳይ ያድርጉ #

 1. ከላይ እንደተጠቀሰው የምርት ጊዜው የሚያበቃበት ባህሪ መንቃቱን ያረጋግጡ።
 2. ወደ የክፍያ መጠየቂያ አታችመንት አቀማመጥ ደረሰኝ ማስተካከያዎች ጋር ይሂዱ እና የማለቅያ ቀን ግዜን አሳይ የሚለውን ሳጥን ያንቁ
 3. የግዢ ወይም የመክፈቻ ክምችት ሲመዘገብ እቃው የሚያበቃበት ቀን ከተመዘገበ በሃላ ሽያጮች በሚከናወንበት ሰአት የእቃው ጥራት ጊዜ የሚያበቃበትን የዝርዝር አማራጭ ያሳያል። መሸጥ የሚፈልጉትን የማለቂያ ቀን የደረሰበትን እቃ ይምረጡ። ከዚያም በህትመት ደረሰኝ ውስጥ፣ የሚያበቃበትን ቀን ያሳያል።

Powered by BetterDocs