የአገልግሎት ዓይነቶች

የአገልግሎት ዓይነቶች #

  1. የአገልግሎት ዓይነቶች በአብዛኛው በሬስቶራንቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ, ለምሳሌ ቦታ አስይዘው, በሬስቶራንት ዴሊቨሪ, 3ተኛ ወገን ዴሊቨሪ አገልግሎቶች ወዘተ.
  2. በአገልግሎት ዓይነት ላይ በመመስረት የአገልግሎት ዓይነቶችን ከሽያጭ ቡድን ጋር በማገናኘት የእቃውን ዋጋ መለወጥ ይችላሉ።
  3. የማሸጊያ ክፍያዎችን ማከል ይችላሉ (ቋሚ ወይም መቶኛ)
  4. እንዲሁም፣ እንደ ብጁ መስኮች ያሉ ተጨማሪ መረጃዎችን ማከል ይችላሉ።

የአገልግሎት ዓይነቶችን ስራ ላይ ማዋል #

ወደ ማስተካከያ -> የድርጅት መረጃ ማስተካከያ -> ሞጁሎች -> “የአገልግሎት ዓይነቶችን” ይመልከቱ

እና ያስቀምጡ

አዳዲስ የአገልግሎት ዓይነቶችን ማስገባት. #

  1. ለምስገባት ወደ ማስተካከያ -> የአገልግሎት አይነቶች -> አክል ይሂዱ
  2. ስም ፣ መግለጫ ያክሉ
  3. ለእያንዳንዱ ቦታ ተፈጻሚ የሚሆነውን የዋጋ ቡድን ይምረጡ። በነባሪ የምርት ዋጋ ለመሸጥ ነባሪ የመሸጫ ዋጋን ይምረጡ።
  4. የማሸጊያ ክፍያ አስገባ፣ የማይተገበር ከሆነ ባዶ ይተው።
  5. ብጁ መስክን ያንቁ፡ ይህ አንዳንድ ብጁ መስኮችን በPOS ስክሪን ውስጥ በአገልግሎት አይነት ላይ ያስችላል።

በPOS/የሽያጭ ስክሪን ላይ የአገልግሎት አይነት መጠቀም፡- #

  1. የአገልግሎት ዓይነቶችን በPOS ስክሪን ስራ ላይ ማዋል ላይ የአገልግሎት ዓይነትን የመምረጥ አማራጭን ታያላቹ።
  2. ሽያጭ ከማስገባቶ በፊት የአገልግሎቱን አይነት ይምረጡ እና ተዛማጅ ዝርዝሮችን ያስገቡ።
  3. ከክፍያ መጠየቂያ አቀማመጥ ላይ ስራ ላይ በማዋል የአገልግሎት አይነት መረጃን በደረሰኝ ላይ ማሳየት ይችላሉ።

Powered by BetterDocs