Table of Contents
#
የስራ ሚናዎች ማስገባት #
- እያንዳንዱ አዲስ ድርጅት ከተወሰኑ መደበኛ የስራ ሚናዎች ጋር አብሮ ይመጣል ከነኚህም መሀከል እንደ፡ አስተዳዳሪ እና ገንዘብ ተቀባይ ተጠቃሽ ናቸው።
አስተዳዳሪ በመተግበሪያው ውስጥ ሁሉም ፈቃዶች አሏቸው።
ገንዘብ ተቀባይ የPOS ክፍል ብቻ ፍቃድ አላቸው። - ያስገቡ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ሚና መፍጠር ይችላሉ ፡የሚና ስም በመስጠት እና ለዚያ ሚና ተገቢውን ፈቃድ በመምረጥ የስራ ዘርፍ መመደብ ይችላሉ።
- አንዳንድ ጊዜ ለተጠቃሚው የአንድ የተወሰነ ቦታ መዳረሻ ፍቃድ ብቻ መስጠት ሊኖርቦት ይችላል። በዚህ ግዜ ቦታዎችን ይገልገሉ ከሚለው አማራጭ ላይ የተፈለገውን መምረጥ ይቻላል። ለድርጅቶ ሁሉንም አካባቢዎች ለማዳረስ ፍቃድ ለመስጠት «ሁሉም ቦታዎች» የሚለውን ይምረጡ።
- የስራ ሚና ፈቃዶች ሊሰጡ እና ሊሰረዙ ይችላሉ።
ማስታወሻ፡ ሚናን ከመሰረዝዎ በፊት የነባር ተጠቃሚን ሚና ማደስ አለብዎት።