Table of Contents
ማንኛውም ግለሰብ አቅራቢ ፣ ደንበኛ ወይም ሁለቱም (አቅራቢ እና ደንበኛ) ሊሆን ይችላል።
አቅራቢዎችን እና ደንበኞችን ማስገባት #
- ወደ አድራሻ መገኛ ይሂዱ ፡ (አቅራቢዎች ወይም ደንበኛ)
- አዲስ መገኛ አስገቡ የሚለውን ቁልፍ ይጠቀሙ። የግለሰብ መገኛውን አይነት ይምረጡ ፡ አቅራቢ / ደንበኛ ወይም ሁለቱም።
- በተመረጠው መገኛ አይነት መሰረት ፡ ተዛማጅ መስኮችን ያሳያል። ተዛማጅ ዝርዝሮችን ይሙሉ።
- ተጨማሪ መስክ ለማየት ተጨማሪ መረጃ የሚለውን ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ።
- የክፍያ ውሎች፡ ይህ መተግበርያው ለአቅራቢዎች እና ለደንበኞች በመጠባበቅ ላይ ያሉ ክፍያዎችን ለእርስዎ ለማሳወቅ ይረዳል። በሁለት አማራጭ ማለትም በቀናት ወይም በወራት ውስጥ የክፍያ ጊዜን መግለጽ ይችላሉ።
- የደንበኛ ቡድን፡ ዝርዝሮችን እዚህ ያንብቡ።
- የብድር ገደብ፡ ይህ ለደንበኛው ሊሰጥ የሚችለው ከፍተኛው የብድር መጠን ነው። በማንኛውም ሽያጮች ውስጥ ክሬዲቱ ከዚህ መጠን በላይ ከሆነ በዱቤ መሸጥን አይፈቅድም።
- የመክፈቻ ቀሪ ሒሳብ፡ ዘመናዊ ነጋዴ መተግበርያውን መጠቀም ከመጀመርዎ በፊት የደንበኛ ወይም አቅራቢ ቀሪ ሂሳብ መክፈት። ስለዚህ የቀደመ ቀሪ ሂሳብ ካለ እዚህ ማከል ይችላሉ።
- የቅድሚያ ሒሳብ፡ አንዳንድ ጊዜ ደንበኛ፨አቅራቢ ክፍያ፨ አስቀድሞ ገንዘብ ይከፍላሉ ወይም ይወስዳሉ። ይህ በደንበኛው፨አቅራቢው የሚከፈለውን ወይም የሚወስደውን የቅድመ ክፍያ ቀሪ መጠን ያሳያል።
አቅራቢዎችን እና ደንበኞችን መረጃ ለመመልከት #
- ስለ አቅራቢ ወይም ደንበኛ ዝርዝሮችን ለማየት የእይታ ቁልፍን ጠቅ ያድርጉ። ለዚያ መገኛ ሙሉ ዝርዝሮችን ከሚመለከታቸው ግብይቶች (ግዢዎች እና ሽያጮች) ጋር ያሳያል።
- ቀሪ ክፍያ የሚከፈልበት መጠን፡ ለደንበኛ ወይም ለአቅራቢው ተገቢውን መጠን ለመክፈል ይህንን ቁልፍ መጠቀም ይችላሉ። ይህ የሁሉንም ደረሰኞች አጠቃላይ ክፍያ መጠን ይከፍላል።