የሎጥ ቁጥር #
የሎጥ ቁጥር ምንድን ነው? #
ሎጥ ቁጥር እቃዎች ሲመረቱ በምድብ የተመደቡ ተከታታይ ቁጥሮች ናቸው። ይህ ቁጥር በተመሳሳይ ሎጥ ውስጥ የሚመረቱትን እቃዎች ለመከታተል የሚያገለግል ሲሆን የጥራት ማረጋገጫ እና የእቃ ዝርዝር አያያዝን ይረዳል።
የሎጥ ቁጥር ስራ ላይ ማዋል #
የሎጥ ቁጥር ስራ ላይ ለማዋል ወደ ማስተካከያዎች ፡የድርጅት መረጃ ማስተካከያ ፡በመቀጠል ግዢዎች ጋር ይሂዱ
የሎጥ ቁጥርን ይፍቀዱ አመልካች ሳጥኑን ያረጋግጡ በመቀጠል ማስተካከያውን ያድሱ።
በግዢዎች ምልከታ ገፅ ውስጥ የሎጥ ቁጥርን ማስገባት #
የሎጥ ቁጥሩ ከላይ እንደተገለፀው ፍቃድ ከተሰጠው የግዢ ክምችት ሲያስገቡ የሎጥ ቁጥሩን ለማስገባት የሚያስችል የሎጥ ቁጥር መስክ ያሳያል።
ከተፈለገው ሎጥ ላይ ብቻ መሸጥ #
የ POS ሽያጭ አጠቃቀም ማብራርያ ሰነድ(Documentation) የሎጥ ቁጥር መግለጫ እዛ ላይ ይመልከቱ።
በክፍያ መጠየቂያ አታችመንት ላይ የእቃውን ሎጥ ቁጥር ማሳየት #
- ከላይ እንደተጠቀሰው የሎጥ ቁጥር ባህሪ መፈቀዱን ያረጋግጡ።
- ማስተካከያዎች ፣ የድርጅት መረጃ ማስተካከያ በመቀጠል ግዢዎች ወደሚለው ይሂዱ እና የሎጥ ቁጥርን ይፍቀዱ ሚለውን ሳጥን ይምረጡት
- የግዢ ወይም የመክፈቻ ክምችት ሲመዘግቡ የሎጥ ቁጥሩ ከገባ ሽያጮችን በሚያከናውኑበት ጊዜ የሎጥ ቁጥሩን እና የምርት ጊዜው የሚያበቃበትን ዝርዝር ያሳያል። ለመሸጥ የሚፈልጉትን የሎጥ ቁጥር ይምረጡ። ከዚያም በህትመት ደረሰኝ ውስጥ የሎጥ ቁጥር ያሳያል።