እቃዎችን ማስገባት #
- ወደ እቃዎች የማውጫ ዝርዝር ይሂዱ በመቀጠል እቃዎች ያስገቡ ሚለውን አማራጭ ይጠቀሙ
- የእቃ ስም ያስገቡ
- ብራንድ
- መስፈርያ
- ምድብ
- የበታች ምድብ:
- SKU፡ ምርቱን ለመለየት የሚያገለግል ልዩ SKU ያስገቡ እና ባርኮድ በመለያዎች ውስጥ ያትሙ። በራስ ለማመንጨት ባዶ ይተዉት። እንዲሁም በራስ-የመነጨ SKU ቅድመ ቅጥያ ማስገባት ይችላሉ።
- የባር ኮድ አይነት፡ የባር ኮድ አይነት ይምረጡ፣ መደበኛ/የሚመከር የC128 አማራጭ ነው። የገባው እቃ አስቀድሞ SKU ቁጥር ካለው ብቻ እንዲቀይሩ እንመክራለን።
- የማይሸጡ እቃዎች፡ አንድ እቃ የማይሸጥ ከሆነ በPOS ወይም በሽያጭ ስክሪን ላይ አይታይም። ይህ ለአንዳንድ እቃዎች መሸጥን በጊዜያዊነት ማገድ ከፈለጉ ወይም የፋብሪካ አስተዳደር ተጠቃሚ ደንበኛ ከሆኑ ለምሳሌ እንደ ጥሬ እቃዎች ያሉ ምርቶችን የማይሸጥ ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው።
- አነስተኛ ብዛት ማስታወሻ፡ የቀሩት የእቃ ክምችቶች ወደ ተቀመጠው አነስተኛ ብዛት ቁጥር ደረጃ ወይም ከዚህ በታች ሲደርሱ የ አነስተኛ ብዛት ማስታወሻ እንዲያገኙ ይረዳዎታል።
- የእቃ ክምችት ያስተዳድሩ፡ የክምችት አስተዳደርን በእቃ ምዝገባ ደረጃ ይፍቀዱ/ይከልክሉ። እንደ ጥገና አገልግሎት፣ የውበት ሳሎን፣ የድረገፅ ግንባታ እና ህትመት ላሉ አገልግሎቶች የእቃ ክምችት አስተዳደር አያስፈልግም። ስለሆነም የእቃ ክምችት አስተዳደርን ፍቀዱ ሚለውን ምርጫ ባዶ በመተው፣ ገደብ በሌለው መጠን መሸጥ ይችላሉ። እነኚን መሰል አገልግሎቶች ሚሰጡ ተቋማት ዘመናዊ ነጋዴን በመጠቀም ስራቸውን ማስተዳደር ይችላሉ።
- የእቃ ስም ያስገቡ
- የንግድ ቦታ፡ ይህ እቃ የሚሸጥበት ወይም የሚገዛበትን የንግድ ቦታ(ዎች) ይምረጡ።
- ለዚያ ምርት የሚመለከተውን የታክስ ወይም ቫት አይነት ይምረጡ። ቫት ማስገባት
- የእቃ አይነት፥
ነጠላ እቃ #
- ምንም አይነት ልዩነት ለሌላቸው እቃዎች ተፈጻሚ ይሆናል። ስለሆነም የእቃ አይነት ሚለው ላይ ነጠላ የሚለውን ይምረጡ
- ነጠላ እቃን በሚመርጡበት ጊዜ ፡ ታክስን ጨምሮ ወይም ሳይጨምር የመደበኛውን የእቃ ዋጋ ማስገባት አለቦት ትርፍ መጠን መቶኛ % (ከማስተካከያዎች ውስጥ የድርጅት መረጃ ማስተካከያ ላይ በመግባት መደበኛ የትርፍ መጠን ማዘጋጀት ይችላሉ ፡ ፤ ይህ በእያንዳንዱ እቃ ምዝገባ ላይ ሚፈልጉትን % ለመሙላት ይረዳል)። በትርፍ መጠን ላይ በመመስረት ቫትን ሳያካት የመሸጫ ዋጋን በራስ፡ሰር ያሰላል። እንዲሁም የመሸጫ ዋጋውን እራስዎ ማስገባት ይችላሉ እና በራስ፡ሰር የትርፍ መጠን መቶኛን ያስተካክልሎታል።
ተለዋዋጭ እቃ #
- ልዩነት ላላቸው እቃዎች የሚተገበር ሲሆን (እንደ መጠን ወይም ቀለም ወይም ዲዛይን ወይም ጣዕም ወዘተ) የልዩነት አይነቶችን ለመፍጠር መጀመርያ ወደ እቃዎች ሚለው ማውጫ በመሄድ አማራጮች ላይ ልዩነቶችን መግለጽ ይችላሉ። ልዩነትን የመፍጠር ጥቅሙ ተመሳሳይ ልዩነቶችን ለተለያዩ እቃዎች ላይ ለማስገባት ሳይቸገሩ ጊዜን መቆጠብ ያስችላል።
- ተለዋዋጭ ምርትን በሚመርጡበት ጊዜ ፡ ሁሉንም ልዩነቶች እና ተዛማጅ የግዢ ዋጋን፣ የመሸጫ ዋጋን ለማስገባት የተለያዩ መስኮችን ያሳያል። ከምርጫዎቹ ውስጥ ልዩነቶቹን መምረጥ አለብዎት እና ለዚያ አምሳያ ልዩነቶቹን በራስ፡ሰር ይሞላል። የተለዋዋጭ ስም ፣ ልዩነት አይነት መለወጥ ይችላሉ።
- ለሁሉም የእቃ ልዩነቶች ተመሳሳይ የግዢ ዋጋ ወይም የመሸጫ ዋጋ ወይም ትርፍ መጠን ለመስጠት በመጀመሪያው ልዩነት ውስጥ የሚገኘውን ድርብ ምልክት ቁልፍ ይጫኑት።
- ልዩነቶችን ስለማስገባት የበለጠ ያንብቡ
ጥምር ወይም ጥቅል እቃ #
ጥምር እቃ ማስገባት
- ጥምር እቃ የጥቅል እቃዎችም ይባላሉ።
- በርካታ እቃዎችን እንደ አንድ ጥምር ምርት እየቀረበ ነው።
ለምሳሌ “የተሟላ ኮምፒተር ” እቃ፡ 1 ፒሲ ሞኒተር + 1 ፒሲ ሲፒዩ + 1 ፒሲ ኪቦርድ + 1 ፒሲ ማውስ ሊኖረው ይችላል።
ስለዚህ አንድ ሰው ኮምፒውተር ሲገዛ ሁሉንም እቃዎች በውስጡ ያገኛሉ። - የታሸገው እቃ ክምችት በዚያ ጥቅል ውስጥ ባሉ የግል እቃዎች ክምችት ላይ የተመሰረተ ነው።
ምሳሌ፡ 5 ኮምፒውተር ሞኒቶር፣ 4 ሲፒዩ ፣ 10 ኪቦርድ፣ 50 ማውስ፣ የኮምፒዩተር ስብስብ ክምችት 4 ፒስ (ኮምፒተር) ይሆናል። - የጥቅል እቃው በሚሸጥበት ጊዜ በውስጣቸው ያሉት ሁሉም እቃዎች ክምችት በራስ፡ሰር ይቀነሳል።
- በጥቅል እቃ ውስጥ ያሉ የነጠላ እቃዎ እንዲሁ ለየብቻ ሊሸጡ ይችላሉ።
- የጥቅል እቃዎች ሊገዙ አይችሉም፣ በውስጡ የሚገኙ ነጠላ እቃዎች ብቻ ሊገዙ ይችላሉ።
ያስገቡ ሚለው ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
እቃን ማስተካከል ይችላሉ። እንዲሁም ወደ CSV፣ PDF ወይም EXCEL ፋይል መቅዳት/መላክ ይችላሉ።
ከተለያዩ ልዩነቶች ጋር እቃዎችን ማስገባት #
ብዙ ልዩነቶችን የሚያካትቱ እቃዎች ካሎት ለምሳሌ ሸሚዝ የቀለም እና የመጠን ልዩነት ሊኖረው ይችላል፣ ከነዚ መሰል እቃዎች ጋር ለመስራት የሚያስችል መንገዶች አሉን፦
መፍትሄ 1፣ ጥምር ልዩነት መፍጠር፡፡ “ቀለም ፣ መጠን” የሚል ስም ያለው ልዩነት እና እንደ ቀይ፡ትንሽ፣ ቀይ፡መካከለኛ፣ ቀይ፡ትልቅ፣ ወዘተ ያሉ መግለጫዎችን መጨመር ይችላሉ፣ ይህ ሸሚዙን ሲመዘግቡ ሊሞላ ይችላል።
መፍትሄ 2፣ በርካታ አማራጮችን ይፍጠሩ፥ እንደ ሸሚዝ፡ቀይ፣ ሸሚዝ፡አረንጓዴ፣ ሸሚዝ፡ሰማያዊ ያሉ የተለያዩ ምርቶችን ይፍጠሩ በመጠን እንደ ልዩነቶች። ብዙ እቃዎችን ሲመዘግቡ ተመሳሳይ ዝርዝሮችን ብዙ ጊዜ ማስገባት አይኖርብዎትም፣ በመጀመሪያ፣ ሸሚዙ፡ቀይ ከሁሉም የመጠን ልዩነቶች ጋር ይጨምሩ እና ከዚያ የተባዛ እቃ ውሂቡን ለመቅዳት ይጠቀሙ።
የበርካታ እቃዎችን ቦታ በአንድ ጊዜ መመደብ/ማስወገድ #
ወደ እቃዎች ዝርዝር ይሂዱ እና ይህንን ከስር የተቀመጠውን ምስል እንደ ማመሳከርያ ይመልከቱ።
እቃን በሽያጭ ላይ እንዳይውል ማገድ እና መፍቀድ #
የታችኛውን ምስል ይመልከቱ
የእቃ ባርኮድ መጠቀም #
ጥያቄ፡
ለእያንዳንዱ እቃ አዲስ ከመፍጠር እና ከማተም ይልቅ የምርቱን ባር ኮድ እንዴት መጠቀም እንችላለን?
ለእያንዳንዱ እቃ አዲስ ከመፍጠር እና ከማተም ይልቅ የምርት ብራንድ ባር ኮድ እንዴት መጠቀም እንችላለን?
መልስ፡
አንድ እቃ በሚፈጥሩበት ጊዜ በ POS እስክሪን ውስጥ የእቃውን ባርኮድ ቁጥር ያስገቡ። ይህ ባር ኮድ እንደ POS፣ ሽያጭ፣ ግዢዎች፣ ሪፖርቶች እና ሌሎች ባሉ በሁሉም ስክሪኖች ውስጥ ያለውን እቃ ለመለየት ስራ ላይ ይውላል።
ባር ኮድ ያለው እቃ እንዴት ማስገባት ይቻላል? #
አስቀድመው ባርኮድ ያላቸውን እቃዎች ለማስገባት፣ሌሎች እቃዎችን እንደማስገባት ተመሳሳይ እርምጃዎችን ይከተሉ።
- እቃዎች በመቀጠል እቃ ያስገቡ ሚለውን ምርጫ ይምረጡ
- ሁሉንም የእቃ ዝርዝሮች ይሙሉ
- ማሳሰብያ፥ በመለያ ኮድ መሙያ ውስጥ መለያ ኮዱን እስካን አርገው ያስገቡ ወይም የእቃውን ባር ኮድ በመፃፍ ያስገቡ።
የእቃውን መጠን ማስገባት ወይም የእቃ ክምችት መሙላት #
ድርጅቶን ስልታዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር፣ የእቃ መጠን በ3 መንገዶች ማስገባት ይቻላል፡፡
- የመክፈቻ ክምችት በመመዝገብ
- ግዢዎችን በመመዝገብ
- ለእቃ አምራቾች ጠቃሚ፣ ነገር ግን የዚን መፍትሄ ለመጠቀም የፋብሪካ አስተዳደር ፓኬጅ ያስፈልጎታል።