ስያሜዎችን ማተም

ዘመናዊ ነጋዴ ለእቃዎች ብጁ መለያዎችን ለማተም አብሮ ከተሰራ ባህሪ ጋር አብሮ ቀርቧል።

ከተለያዩ ገፆች ወደ የህትመት ማተሚያ ማያ ገጽ መሄድ ይችላሉ፡

ከአማራጮች ውስጥ እቃዎች በመቀጠል መለያዎች ማተም ወደሚለው ይግቡ
ወደ እቃዎች ዝርዝር ይሂዱ ፡ሚፈልጉት እቃ ላይ ድርጊት ሚለውን በመምረጥ መለያዎች ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህ የተመረጠውን እቃ ወደ የህትመት መለያ ዝርዝር ያስገባዎል።
ወደ ግዢዎች በመቀጠል ዝርዝር ግዢዎች ይሂዱ እና ድርጊት ሚለውን በመምረጥ መለያዎች ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህ የተመረጠውን እቃ ወደ የህትመት መለያ ዝርዝር ያስገባዋል።

መለያዎች ማተም #

  1. አንዴ በመለያ ማተምያ ስክሪን ላይ ከገባች ሁ በኋላ የሚፈልጉትን እቃ ስም ወይም ባርኮድ፨መለያ ኮድ በማስገባት መለያዎችን ማተም ይችላሉ።
  2. የእያንዳንዱን እቃ መለያ ሚታተመውን ብዛት (የመለያዎች ቁጥር) ያስተካክሉ።
  3. በስያሜዎች ውስጥ ለማሳየት ሚፈልጉትን ለመምረጥ መረጃ በሚለው ርዕስ ስር ያሉትን አማራጮች በመጠቀም በመለያዎች ውስጥ ለማሳየት የሚፈልጉትን መረጃ ይምረጡ።
  4. በተለጣፊ እስቲከሮች መሰረት የባርኮድ ማስተካከያ ይምረጡ። በመደበኛነት ስራ ላይ የሚውሉ ማስተካከያዎችን አካተናል።
  5. ማስተካከያዎች በመቀጠል ባርኮድ ማስተካከያ ውስጥ አዲስ አቀራረብ ማስገባት ይችላሉ።
  6. መለያዎቹን ለማየት ማየት ሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
  7. ሁሉም ነገር ጥሩ ሆኖ ከተገኘ እሱን ለማተም የህትመት ቁልፍን ጠቅ ማድረግ ይችላሉ።
    ማስታወሻ፡ የህትመቱን የቦታ ስፋት በድረገፅ ማሰሻ ህትመት መስኮት ውስጥ ወደ ‘መደበኛ’ ማስተካከል አለቦት።
    በተለጣፊ እስቲከር መጠን ምክንያት አንዳንድ መረጃዎች በግማሽ እየታዩ ከሆነ እነሱን መደበቅ ይመከራል ወይም በ አንድ ህትመት 20 እስቲከሮችን መጠቀም የተሻለ ነው።

ስህተት፥ ለተመረጠው ባርኮድ አይነት የማይደገፍ መለያ ኮድ አስገብተዋል #

ይህ ስህተት ማለት እቃውን በሚመዘግቡበት ጊዜ በእርስዎ የቀረበው የመለያ ኮድ ለባርኮድ ኢንኮዲንግ አይነት አይስማማም።

መፍትሄው የእቃውን መረጃ ማደስ እና የባርኮድ አይነት ወደ “code128” ማስተካከል እና መለያውን እንደገና ለማተም መሞከር ይቻላል።

Powered by BetterDocs