መሸጥ (POS ስክሪን)፣ የዱቤ ሽያጭ፣ ረቂቅ ዋጋ ተመን እና የታገዱ ሽያጮች

በPOS ስክሪን ውስጥ የግንኙነት ነጥቦች

እቃዎች መሸጥ፣ የእቃ ዋጋ መቀየር፣ ታክስ እና ቅናሽ፣ የሎጥ ቁጥር እና የማብቅያ ግዜ #

ወደ – መሸጥ -> POS ይሂዱ

ደንበኛ መምረጥ፡ #

በመደበኛነት, “Walk-In Customer” ሚል አለ. ደንበኛን በስም/በደንበኛ መታወቂያ ወይም በስልክ ቁጥር መፈለግ ወይም የፕላስ (+) ቁልፍን ጠቅ በማድረግ አዲስ ደንበኛ ማከል ይችላሉ ።

እቃ መፈለግ እና ማስገባት #

የእቃ ስም ያስገቡ ወይም እቃውን ለመፈለግ ባርኮዱን ይቃኙ። ብዙ እቃዎች ከተጣመሩ የእቃዎቹን አማራጮች ያሳያል, እቃውን ከእሱ ይመርጣል. ወይም አንድ ነጠላ እቃ ካለ በቀጥታ ወደ ዘንቢሉ ይታከላል።

ለአንድ እቃ የእቃ ዋጋ፣ ታክስ / ቫት እና ቅናሽ መቀየር #

እቃዎቹ ከተመዘገቡ በኋላ የእቃ ዋጋን፣ ታክስን / ቫት እና ቅናሾችን ለመቀየር በእቃው ስም ላይ ጠቅ ያድርጉ።
ማሳሰቢያ፡- በእቃዎች ውስጥ የተለያዩ ቫት የመከፈል አማራጭ ከተፈቀደ ብቻ ይታያል
የሽያጭ ላይ ቫት ተፈቅዷል። ከድርጅት መረጃ ማስተካከያ ላይ -> ታክስ ላይ በመሄድ -> በሽያጭ እና ግዢ ሰአት ላይ ታክስ ስሌት መፍቀድ ይችላሉ።

ለአንድ እቃ የሎጥ ቁጥር መምረጥ #

የሎጥ ቁጥር ከነቃ የሎጥ ቁጥርን የመምረጥ ምርጫን ያሳያል። (የሎጥ ቁጥርን መፍቀድ)

ለአንድ እቃ ጥራት የሚያበቃበትን ጊዜ መምረጥ #

  • ጥራት ሚያበቃበት ቀን፡ ጊዜው የሚያበቃበት ቀን ስራ ላይ ከዋለ የሎጥ ቁጥርን የመምረጥ ምርጫ ያሳያል። (የማብቂያ ጊዜን ስራ ላይ ማዋል)

ሽያጮችን ማቋረጥ #

ሽያጮችን ለመሰረዝ የሰርዝ ቁልፍን ጠቅ ያድርጉ። ግብይታቸው የተሰረዙ ሽያጭ ደረሰኞች አይመዘገቡም፣ ስለዚህ ምንም የእቃ ክምችት አይቀነስም።

የክፍያ መጠየቂያውን ለማጠናቀቅ የክፍያ አይነቱን ይምረጡ።

ሽያጩ ሲመዘገብ የክፍያ መጠየቂያ አታችመንት ማተም አማራጭን ያሳያል።

ማሳሰቢያ: ደረሰኝ በትክክል እንዲታተም – የ Margins አማራጮች ወደ “እንደ መደበኛ” መስተካከል አለባቸው.

የሽያጭ ዝርዝር ከሽያጭ አማራጭ -> ዝርዝር ሽያጭ  ሽያጭ አማራጭ ላይ በመሄድ ሊታይ ይችላል።

የሽያጭ ተመን ረቂቆች ሽያጭ -> ዝርዝር ረቂቆች በሚለው ማውጫ ላይ ሊታዩ ይችላሉ።

ማናቸውንም ለውጦች ለማድረግ ከተፈለገ ሁለቱም ሽያጮች እና ረቂቆች ሊታረሙ ይችላሉ።

ፈጣን የተሟላ ክፍያ፡ ፈጣን የተሟላ ክፍያ ማለት ሽያጩ 100% እንደተከፈለ ምልክት ይደረግበታል እና የመክፈያ ዘዴው ጥሬ ገንዘብ ይሆናል። የተለየ የክፍያ ስክሪን አይታይም። የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ ማተም በድርጅት መረጃ ማስተካከያ ላይ የተመሰረተ ነው.

100% የብድር ሽያጭ #

  • በብድር ለደንበኛው ለመሸጥ መጀመሪያ ይህንን ቁልፍ ፍቃድ መስጠት ያስፈልጋል። ወደ ማስተካከያ -> የንግድ መረጃ ማስተካከያ በመቀጠል -> POS -> የዱቤ ሽያጭ መክፈቻ በተን ይከልክሉ ሚለው ሳጥን በመደበኛነት የተመረጠ ስለሚሆን ሳጥኑን በመንካት ምርጫውን ያጥፉት
  • ከዚያ በPOS ስክሪን ላይ “የብድር ሽያጭ” የሚለውን ቁልፍ ማየት ይችላሉ፣በዱቤ ለመሸጥ በቀላሉ ይህንን ቁልፍ ይጫኑ።

የግማሽ ብድር እና የግማሽ ክፍያ ሽያጮች፡- #

ለምሳሌ የክፍያ መጠየቂያ መጠኑ 10,000 ብር ነው እንበል፣ ደንበኛዎት 7000 ጥሬ ገንዘብ እና 3000 ብር በእሱ ላይ ዱቤ እንዲያዝበት፣ ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተሉ።

  1. ባለብዙ አይነት ክፍያ ቁልፍን ጠቅ ያድርጉ
  2. የመክፈያ ዘዴን ይምረጡ እና በደንበኛው የተከፈለውን መጠን ያስገቡ. (ምሳሌ 7000 ብር)
  3. ክፍያ ያጠናቁ ሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
  4. አሁን፣ በመጠባበቅ ላይ ያለው መጠን በእሱ ላይ እንደ የብድር መጠን (ወይም ከደንበኛው የሚወሰድ መጠን) በራስ-ሰር ይታከላል

የሽያጭ ረቂቅ እና ተመን #

ከሽያጭ በፊት ለደንበኛዎ የዋጋ ተመን ለማዘጋጀት ከፈለጉ ይህ ጠቃሚ ነው።

ሽያጩን እንደ ረቂቅ ወይም የዋጋ ተመን ምልክት ማድረግ ያለውን የእቃ ክምችት አይቀንሰውም።

ሁሉንም ተመኖች እና ረቂቆች ከዝርዝር ተመን ወይም ከዝርዝር ረቂቅ በቅደም ተከተል ማየት ይችላሉ። ነባር ረቂቅ/ተመን እንደ የመጨረሻ ሽያጭ ተደርጎ ሊስተካከል ይችላል።

የተቋረጠ ሽያጭ #

የተቋረጠ ሽያጭ ማለት ያልተጠናቀቀ ሽያጭ ወይም ሽያጭ መያዝ ማለት ነው።
የተቋረጠ የሽያጭ ክምችት ካለ የእቃውን ክምችት ይቀነሳል። በስክሪኑ ላይኛው ቀኝ (ከቀን በላይ) የሚገኘውን ቢጫ ቀለም ቁልፍ ጠቅ በማድረግ ሁሉንም የተቋረጡ ሽያጮች ማየት ይችላሉ።

አንዳንዶች የተቋረጠ ሽያጮችን ጉዳይ ይጠቀማሉ #

  1. በግሮሰሪ መደብር ውስጥ፣ የተቋረጡ ሚለውን ቁልፍ ጠቅ ካደረጉ፣ የተወሰኑ የደንበኞችን ሽያጮችን ማቋረጥ እና ሌላ ደንበኛን ማስተናገድ ይችላሉ፣ ተመልሶ ሲመጣ ሽያጩን መቀጠል ይችላሉ።
  2. በሬስቶራንቱ ውስጥ የደንበኞችን ትዕዛዝ ገና ካልተከፈለ ማቋረጥ እና በልተው ሲጨርሱ እና ትዕዛዙን ሲከፍሉ ማጠናቀቅ ይችላሉ፣ ስለዚህ ወደ መጨረሻው ሽያጭ መቀጠል ይችላሉ። ጠረጴዛ 1 ፣ ጠረጴዛ 2 ፣ ጠረጴዛ 3… ከፋፍለው ማስቀመጥ ይችላሉ ስለዚህ ሲጨርሱ ጠረጴዛ 3 መከፈሉን ለመለየት ቀላል ነው።
  3. በሆቴሉ ውስጥ ብዙ ደንበኞች ለ 2 ምሽቶች ቆይተው ገብተው አንዳንድ ምግቦችን ካዘዙ በሃላ ደንበኞች ወደ ክፍል 024 ብቻ ቢሉን ያስከፍሉ ሊሉ ይችላሉ. ስለዚህ ትዕዛዛቸውን ማቋረጥ እና አንዳንድ ተጨማሪ ትእዛዝ ካለ ማስተካከል እና እንደገና ማቋረጥ ይችላሉ። እስከ መጨረሻው ድረስ ሂሳባቸውን ሲከፍሉ የተቋረጠውን ትዛዝ ማጠናቀቅ ይችላሉ። በሆቴል፣ ምሳሌ በማጣቀሻ ቁጥር፡- ክፍል 009 ክፍል 012 የቆዩ ደንበኞች

ካርድ / ብዙ አይነት ክፍያ / ጥሬ ገንዘብ #

ብዙ አይነት ክፍያ፡- ደንበኛው በተለያዩ የክፍያ ዘዴዎች ለምሳሌ የተወሰነ መጠን በካርድ፣ አንዳንዶቹን በጥሬ ገንዘብ እና አንዳንድ የመክፈያ ዘዴዎች መክፈል ሲፈልግ ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ አማራጭ ደንበኛው ትክክለኛው የክፍያ መጠን በላይ በሚከፍልበት ጊዜ እና የተመላሽ ገንዘብ መጠን ለማስላት ይረዳዎታል.
ካርድ፡- ደንበኛው ሙሉውን የክፍያ መጠየቂያ በካርድ መክፈል ሲፈልግ ጥቅም ላይ ይውላል።
ጥሬ ገንዘብ፡- ደንበኛው ትክክለኛውን የክፍያ መጠየቂያ በጥሬ ገንዘብ ሲከፍል ጥቅም ላይ ይውላል። ደንበኛው ትንሽ ወይም ከዚያ በላይ የሚከፍል ከሆነ የክፍያ መጠየቂያው መጠን ከዚያ የለውጥ ተመላሽ ለማግኘት ብዙ አይነት ክፍያን ይጠቀሙ።

ከመገኛ አማራጭ ላይ ክፍያዎችን ማስገባት #

ወደ መገኛ -> አቅራቢዎች ይሂዱ። ለአቅራቢው ድርጊት ላይ ጠቅ ያድርጉ እና “ይክፈሉ” ሚል ያሳያል, በላዩ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና መጠኑን ይክፈሉ. የሚከፈልበት ክፍያ ከሌለ ይህ አማራጭ “ይክፈሉ” ሚለው አይታይም.

የመክፈያ ዘዴን ማስገባት/ማስተካከል ወይም በክፍያ-በኩል #

በክፍያ በኩል /የመክፈያ ዘዴን ያስገቡ/ያስተካክሉ ሚለውን ይከተሉ

የማዞሪያ ሜካኒዝም ለጠቅላላ የሽያጭ መጠን ወይም ጠቅላላ ተከፋይ #

ማዞር የሚከፈለውን አጠቃላይ የገንዘብ ልውውጥ በአቅራቢያው ወዳለው የገንዘብ ልውውጥ ለማጠጋጋት ይረዳል።

ማጠጋጋትን ለመፍቀድ ወደ ማስተካከያ -> የድርጅት መረጃ ማስተካከያ -> ሽያጭ ይሂዱ እና የመጠን ማጠጋግያ ዘዴን ይምረጡ

የመጠን ማጠጋግያ ዘዴ #

ወደ ሙሉ ቁጥር፡- የክፍያውን ዋጋ ወደ ሙሉ ቁጥር ያጠጋጋል። ለምሳሌ 1.49 ወደ 1.00፣ እና 1.51 ወደ 2.00 ይጠጋጋል።
ወደ አስርዮሽ (በርካታ 0.05)፡ የተከፈለውን ዋጋ ወደ ቅርብ የአስርዮሽ ቁጥር ያጠጋጋል ይህም የ0.05 ብዜት። ለምሳሌ 1.49 ወደ 1.50፣ 1.51 ወደ 1.50፣ 1.59 ወደ 1.60፣ 1.54 ወደ 1.55 ይጠጋጋል።
ተመሳሳይ ሁሉም ሌሎች ዙር ወደ አስርዮሽ ቁጥር የሚሠራው እንደ ማባዣው ነው።

 

Powered by BetterDocs