ቀላል እና ዘመናዊ መነገጃ በእጆ ያስገቡ

ላጠቃቀም ቀላል ፣ ያለቦታ ገደብ ባሉበት ሆነው የድርጅቶን አሰራር ይከታተሉ ፣ ያስተዳድሩ!

Play Video

ለሁሉም ኮምፒውተሮች ፣ ታብሌቶች እና ስልኮች ምቹ የሆነ

አሁን ይጀምሩ
ለሁሉም ኮምፒውተሮች ፣ ታብሌቶች እና ስልኮች ምቹ የሆነ
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

አስተማማኝ

አስተማማኝ

ከተለምዶው POS ሲስተም የተሻለ አገልግሎት ያገኛሉ።

የተሟላ መረጃ

ነፃ 14 የመለማመጃ ቀናት ከተሟላ የፅሁፍ እና ቪዲዮ መረጃ

አለማቀፍ

አለማቀፍ

ከሀገር ውስጥም ይሁኑ ከሀገር ውጭ ባሉበት ሆነው የድርጅቶን የስራ ክንውን መከታተል የሚያስችል።

ምቹ

ለሁሉም ተገልጋዮች አቅምን ባማከለና በእጃቸው ላይ ባለ መሳርያ በቀላሉ እንዲሰራ ተደርጎ የተዘጋጀ።

ተመጣጣኝ ዋጋ

ተመጣጣኝ ዋጋ

ድርጅቶን ለማስተዳደር ከሚቀጥሩት ሰራተኛ በላቀ ጥራት እና በዝቅተኛ ደሞዝ ሁሉንም ክንውን ይመዘግባል ፣ ይቆጣጠራል።

ጠንካራ

ጠንካራ

በተለምዶ ኮምፒውተር ላይ ከሚጫኑ POS ከሚያጋጥሞ ችግር መካከል መብራት ሲጠፋ አገልግሎት መቋረጥ ፣ ሲስተሙ በቀላሉ በኮምፒውተር ቫይረስ ከተጠቃ የመረጃ መጥፋት እና ተያያዥ ችግሮች ሁሉ የፀዳ ነው።

በ Cloud Compute የድርጅትዎ አገልግሎት አቅራቢ

ውድ የሆኑ የዴስክቶፕ ወይም ላፕቶም መሳርያዎችን መግዛት ሳይጠበቅቦ እጆ ላይ ባሉ መሳርያዎች ይገልገሉ።
ከትንሽ ነጋዴዎች እስከ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ፣ ለግልም ሆነ ለመንግስት ድርጅቶች ፣ ለትላልቅ ኢንተርፕራይዝ የሁሉንም የስሌት ሀይል (Compute Power) ሚያሟላ ዘመናዊ የኔትዎርክ መረብ!

ለሁሉም ነጋዴዎች

ከጥቃቅን እና አነስተኛ ነጋዴዎች እስከ ትልቅ ሱፐር ማርኬት ፣ ፋርማሲ እና ማንኛውም የንግድ ድርጅት። ከ ግለሰብ አንስቶ ብዙ ቅርንጫፍ ያላቸው ንግድ ድርጅቶች, የሁሉንም አቅም ያማከለ መፍትሄ

ለካፌ ፣ ባር እና ሬስቶራንት ፣ ለሆቴሎች

ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደ ካፌ ፣ ባር እና ሬስቶራንት ፣ ሆቴሎች እና ሌሎችም የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ኩሽና አስተዳደር እና መስተንግዶ ክትትል የመሳሰሉ ልዮ መፍትሄዎች

የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር

እንደ ሪልእስቴት ላሉ ተቋማት እጅግ ጠቃሚና ወሳኝ የደንበኛ ግንኙነት ማስተዳደርያ መተግበርያ ያሟላ ሲሆን የደንበኛዎን የመግዛት አቅምና መች ሊገዙ እንደሚችሉ በመረጃ የተደገፈ የሽያጭ ስራት ለመዘርጋት ያስችላል።

ንብረት አስተዳደር

ለትላልቅ መግስት እና የግል ድርጅቶች ፣ እርዳታ ድርጅቶች ለመሳሰሉ ተቋማት ታስቦ የተዘጋጀ። በቀላሉ የድርጅቶን ንብረት በመመዝገብ ለድርጅቱ ሰራተኞች ፍቃድ መስጠት። ለምሳሌ፥ ኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች ፣ መጓጓዣ መኪና እና የመሳሰሉት። ለሚሰጡት ንብረት በቀላሉ የቀን ገደብ መስጠት ፣ ማገድ እና ሌሎችንም ስራ አቅላይ ቴክኖሎጂዎችን ያሟላ።

ፕሮጀክት አስተዳደር

እንደኮንስትራክሽን ላሉ በጣም ውስብስብ ፕሮጀክቶች በቀላሉ የስራ ክንውን ለመከታተል የሚያስችል። ከሁሉም ሰራተኞች ጋር ባካል መገናኘት ሳያስፈልጎ የፈለጉትን ሰራተኛ የፈለጉት የስራ ዘርፍ ላይ መመደብ ፣ ውጤት መከታተል ፣ የግል እና የቡድን ማስታወሻዎችን መላክ የመሳሰሉ ዘመናዊ መፍሄዎችን የያዘ።

ፋብሪካ አስተዳደር

ለአምራች ድርጅቶች የተዘጋጀ። ከ ፋብሪካ ግብአት ግዢ እስከ ምርት እና ሽያጭ ያለውን የግብአት ፍጆታ እና የግብአት የውህድ ቀመር (Recipe) ፣ ተረፈምርት የመሳሰሉ ስሌቶችን እና የያንዳንዱን ምርት ሙሉ ታሪክ መከታተያ በተጨማሪም የምርት ጥራት ማብቅያ ግዜ የመሳሰሉ ክንውኖችን ማስተዳደር ያስችላል።

ለመሸጥ ፣ ለማስተዳደር ፣ ለሪፖርት እና ለድርጅቶ እድገት ሚያስፈልገውን መፍትሄ የያዘ ዘመናዊ መነገጃ

መሸጥ
ማስተዳደ
ሪፖርት
 እድገት

የድርጅቶን ሽያጭ በቀላሉ ይከታተሉ

እርሶ በስራ ቦታ መገኘት ባይችሉ እንኳን በድርጅቶ ሰራተኞች ሚከናወነውን ሽያጭ ሙሉ መረጃ ባሉበት ሆነው ሽያጩ በሚከናወንበት ቅፅበት መከታተል ይችላሉ። እቃ ለማን እንደተሸጠ ፣ የትኛው ሰራተኛ እንደሸጠ ፣ በምን ሰአት እንደተሸጠ ፣ የሽያጭ ትርፍ በ አንድ እቃም ይሁን ጠቅላላ ትርፍ ሁሉንም መረጃ በኪሶ በያዙት ስልክ ባሉበት ሽያጭ ማከናወን እና ማየት ያስችሎታል።

ድርጅቶን ግዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ያስተዳድሩ

በድርጅቶ ውስጥ ሚከናወኑ ድርጊቶችን በቀላሉ ማስተዳደር ያስችሎታል። ሰራተኞችን ፣ የምርት ክምችት ፣ ወጪ ፣ ገቢ ፣ ትርፍ ፣ ኪሳራ የመሳሰሉ የድርጅቶን ስኬት የሚመዝኑባቸውን መስፈርቶች በቀላሉ በጆ በያዙት ስልክ ባሉበት ሆነው ማስተዳድር ማስቻሉ ግዜ ቆጣቢ እና እጅግ ተመራጭ ያደርገዋል።

አስፈላጊውን ሪፓርት ባስፈለገ ሰአት በእጆ ያገኛሉ

የእቃ ግዢ ፣ የወር እና አመታዊ ሽያጭ ፣ የሰራተኞች ክፍያ ፣ ትርፍ ፣ ኪሳራ ፣ የእቃ ዝርዝር የፈለጉትን መረጃ ባስፈለገበት ቦታ በቀላሉ ከስልኮ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ይህ ቴክኖሎጂ የድርጅት ባለቤቶች መረጃቸውን በወረቀት ሰብስቦ ከመጓጓዝ የሚያድን ከመሆኑም በተጨማሪ በቀላሉ ፕሪንት ወይም በሚፈልጉት ፋይል ፎርማት(PDF,Excel,Word) በተፈለገ ሰአት እንደ አታችመት ለሚፈልጉት ሰው በኢሜል እና በሌሎች አማራጮች መላላክ ያስችላል።

የድርጅቶን እድገት በመረጃ ላይ የተደገፈ አሰራር በመዘርጋት ስኬታማ ያድርጉ

ትንሽም ይሁን ትልቅ ድርጅት በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ላይ ስኬታማ ለመሆን ካሰቡ ዋነኛው የድርጅት የስኬት ሚስጥር በስራ ቦታ ላይ ሚከናወኑትን ድርጊቶች ጠንቅቆ መረዳት ሲቻል ብቻ ነው። ዘመናዊ ነጋዴ ከትንሽ እስከ ትልቅ ላሉ ኢንተርፕራይዞች ይዞ የመጣው የCloud Compute ቴክኖሎጂ የድርጅት ባለቤቶችም ይሁኑ ሰራተኞች በመረጃ የተደገፈ ዘመናዊ አሰራር በድርጅታቸው ላይ ለመተግበር ያስችላል።